እንዲህም አለ፤ “ቸርነቱንና ታማኝነቱን ከጌታዬ ያላጓደለ፣ እኔንም ወደ ጌታዬ ዘመዶች ቤት የመራኝ፣ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።”
መዝሙር 61:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ይንገሥ፤ ይጠብቁት ዘንድ ምሕረትህንና ታማኝነትህን አዘጋጅለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለንጉሥ ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ፥ ዓመታቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! በፊትህ ለዘለዓለም እንዲነግሥ አድርገው፤ በዘለዓለማዊው ፍቅርህና በታማኝነትህ ጠብቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መድኃኒቴ በእግዚአብሔር ነው፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ነው፥ የረድኤቴ አምላክ፥ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው። |
እንዲህም አለ፤ “ቸርነቱንና ታማኝነቱን ከጌታዬ ያላጓደለ፣ እኔንም ወደ ጌታዬ ዘመዶች ቤት የመራኝ፣ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።”
እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሰራዊት ሆኛለሁ።
ስለዚህ ስምህ ለዘላለም ታላቅ ይሆናል፤ ሰዎችም፣ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው!’ ይላሉ። የባሪያህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።
ክርስቶስ የእውነተኛዪቱ ድንኳን ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደ ተሠራችው መቅደስ አልገባም፤ ነገር ግን አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ እርሷ፣ ወደ ሰማይ ገባ።