መዝሙር 6:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴም እጅግ ታወከች፥ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ተመልሰህ ታደገኝ፤ የዘለዓለም ፍቅርህን በማሳየት አድነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ። |
አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት። ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ አልጠበቃችኋቸውምም፤ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘የምንመለሰው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።