20 ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።
20 አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ፥ አንተ ጉልበቴ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
20 ነፍሴን ከሰይፍና ከእነዚያ ውሾች ኀይል አድነኝ።
ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ ዝም ብለህ ታያለህ? ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው፣ ብርቅ ሕይወቴን ከአንበሶች ታደጋት።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣ በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ! እረኛውን ምታ፣ በጎቹም ይበተናሉ፤ እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥተህ ግጠማቸውና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ከክፉዎች ታደገኝ።
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣ በደልም በእጄ ከተገኘ፣
ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ ይፈሩ፤ ይዋረዱም፤ ጕዳቴንም የሚሹ፣ ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ።
ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤ ስለ ጠላቶቼም ተቤዠኝ።
ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ፣ ይፈሩ፤ ይዋረዱም፤ ጕዳቴንም የሚሹ፣ ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ።