Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 17:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥተህ ግጠማቸውና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ከክፉዎች ታደገኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አቤቱ፥ ተነሥ፥ ቀድመህ ወደ ታች ጣለው፥ ነፍሴን ከኃጢአተኛ በሰይፍህ አድናት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ሕይወቴን ከክፉዎች አድን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ማ​ያት አን​ጐ​ደ​ጐደ፥ ልዑ​ልም ቃሉን ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 17:13
16 Referencias Cruzadas  

ተነሥና እርዳን! ስለ ምሕረትህ ስትል ተቤዠን።


ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።


እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!


እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።


ይህም የሆነው የአንተ ክንድና ፈቃድ ጥንት የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።


ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቀድሞው ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ አትሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርድ ሾመኸዋል፤ ዐለት ሆይ፤ ይቀጣ ዘንድ ሥልጣን ሰጥተኸዋል።


የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፤ ተነሥ፤ ተነሥ! ኀይልን ልበስ፤ እንዳለፉት ዘመናት፣ በጥንት ትውልዶችም እንደ ሆነው ሁሉ ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ፣ ታላቁን ዘንዶ የወጋህ አንተ አይደለህምን?


“ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።


እግዚአብሔርና የቍጣው ጦር መሣሪያ፣ ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፣ ከሩቅ አገር፣ ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።


መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው።


“የቍጣዬ በትር ለሆነ፣ የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!


እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕግህ እየተጣሰ ነውና፣ ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው።


እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ አምላክ ሆይ፤ ክንድህን አንሣ፤ ረዳት የሌላቸውንም አትርሳ።


ክፉዎችን የሚቋቋምልኝ ማን ነው? ከክፉ አድራጊዎችስ ጋራ የሚሟገትልኝ ማን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios