መዝሙር 59:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ እግዚአብሔር አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤ በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፥ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነህ፤ ሕዝቦችን ለመቅጣት ተነሥ፤ ክፉ ከዳተኞችን ያለ ምሕረት ቅጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጆችህም፥ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ ስማኝም። |
አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤
ደግሞም እግዚአብሔርም ሙሴን፣ “ ‘የአባቶቻችሁ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤’ “ስሜም ለዘለዓለም ይኸው ነው፤ ወደ ፊት በተከታታይ በሚነሣው ትውልድ ሁሉ የምታሰበው በዚህ ስም ነው ብለህ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው” አለው።
አንተ ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ ሊገድሉኝ ያሤሩብኝን ሤራ ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውን ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህ ወድቀው የተጣሉ ይሁኑ፤ በቍጣህም ጊዜ አትማራቸው።
ንጉሥ ሆይ፤ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ ሌላ ሰውም ሆነ ወደ ሌላ አምላክ መጸለይ እንደሌለበት ንጉሡ ዐዋጅ እንዲያወጣ፣ ትእዛዙም እንዲፈጸም፣ ይህንም የተላለፈ ወደ አንበሶች ጕድጓድ እንዲጣል፣ የመንግሥት የበላይ አስተዳዳሪዎች፣ መኳንንት፣ መሳፍንት፣ አማካሪዎችና አገረ ገዦች ሁሉ በአንድነት ተስማምተዋል።
“እናንተ እስራኤላውያን፣ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር “እስራኤልን ከግብጽ፣ ፍልስጥኤማውያንን ከቀፍቶር፣ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?