የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና፤ በቂ ዋጋም ከቶ ሊገኝለት አይችልም፤
በእውነት ማንም እራሱን አያድንም፥ ማንም ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥
ለሰው ሕይወት የሚከፈለው ዋጋ እጅግ ብዙ ነው፤ የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም።
ስለ መሥዋዕትህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤ የሚቃጠል ቍርባንህም ሁልጊዜ በፊቴ ነው።
ወይስ፣ ‘ከጠላት አስጥሉኝ፣ ከጨካኝም እጅ ተቤዡኝ’ አልኋችሁን?
ጌታ ሆይ፤ ለዳዊት በታማኝነትህ የማልህለት፣ የቀድሞው ምሕረትህ የት አለ?
ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ፣ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው በነፍሱ ምትክ ሊከፍለው የሚችለው ዋጋ ምንድን ነው?