መዝሙር 49:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሬቶችን በስማቸው ቢሰይሙም፣ መቃብራቸው የዘላለም ቤታቸው፣ ከትውልድ እስከ ትውልድም መኖሪያቸው ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቢባን እንደሚሞቱ፥ ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንደሚጠፉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንደሚተዉ አይቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ መሬት በየስማቸው የነበራቸው ቢሆንም እንኳ መቃብር የዘለዓለም ቤታቸውና መኖሪያቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የዱር ውበትም በእኔ ዘንድ አለ። |
አቤሴሎም፣ “ስሜን የሚያስጠራ ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ በራሱ ስም ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፣ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል።
ምክንያቱም ሰው ሥራውን በጥበብ፣ በዕውቀትና በብልኀት ሠርቶ፣ ከዚያ ያለውን ሁሉ ለሌላ ላልለፋበት ሰው ይተውለታል። ይህም ደግሞ ከንቱና ትልቅ ጕዳት ነው።
ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር፣ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ወሰን ድረስ የሚገኘውን መላውን የአርጎብ ምድር ወሰደ፤ ምድሪቱም በስሙ ተጠራች፤ ከዚሁ የተነሣ ባሳን እስከ ዛሬ ድረስ ሓቦት ኢያዕር ትባላለች።
ሳሙኤልም ጧት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፣ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው።