መዝሙር 49:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ! በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ምድርንም ጠራት፤ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ። |
እርሱም፣ “ባሪያዬ መሆንህ፣ የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣ የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።
እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤ ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤ ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ ልዑል እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይመሰክርባችኋል።
“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም ከሚቀበለው ሰው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን፣ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ አደርገዋለሁ።