መዝሙር 47:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚወድደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣ ርስታችንን እርሱ መረጠልን። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብን ከእኛ በታች፥ ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርስት አድርገን የምንይዛትን ምድር መረጠልን፤ ይህችም ምድር ለሚወድደው ለእስራኤል ሕዝብ መመኪያ ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የምድር ነገሥታት ተሰብስበው በአንድነት መጥተዋል። |
“እኔም፣ “ ‘የተመረጠችውን ምድር፣ የትኛውም ሕዝብ ያላገኘውን የተዋበች ርስት ልሰጥሽ፣ እንደ ወንዶች ልጆቼ ምንኛ በደስታ ልቍጠርሽ’ አልሁ፤ ‘አባቴ’ ብለሽ የምትጠሪኝ፣ እኔንም ከመከተል ዘወር የማትዪ መስሎኝ ነበር።
በዚያ ቀን፣ ከግብጽ አውጥቻቸው ከምድር ሁሉ ይልቅ ውብ ወደሆነችው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወዳዘጋጀሁላቸውም ምድር እንደማስገባቸው ማልሁላቸው።
ጌታ እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣ የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም፣ እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ፣ እግዚአብሔር የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል።
“እኔ ወድጃችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት ወደድኸን?’ ትላላችሁ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ያዕቆብን ወደድሁ፤
“በዚያ ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ፤
እንዲሁም በርሱ የተጠራችሁለት ተስፋ፣ ይህም በቅዱሳኑ ዘንድ ያለውን ክቡር የሆነውን የርስቱን ባለጠግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ
ይህች ምድር አምላክህ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፣ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ምን ጊዜም የማይለያት ናት።