“ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፣ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፣ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክታቸውን ከፊቱ አሳድዶ ታላላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?
መዝሙር 44:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤ አንተ ወድደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅህ አሕዛብን አባረረች፥ እነርሱንም ተከልህ፥ አሕዛብን አስጨንቀህ እነሱን አለመለምክ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያል ሆይ፥ በደም ግባትህና በውበትህ፥ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ። |
“ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፣ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፣ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክታቸውን ከፊቱ አሳድዶ ታላላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?
አምላካችን ሆይ፤ የዚህችን ምድር ነዋሪዎች ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት አሳድደህ ያስወጣህና ለወዳጅህ ለአብርሃም ዘሮች ለዘላለም የሰጠሃቸው አንተ አይደለህምን?
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የተላከው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ነገር ግን እግዚአብሔር አባቶችህን ስላፈቀረ፣ ወደዳቸው፤ ዛሬም እንደ ሆነው የእነርሱ ዘር የሆናችሁትን እናንተን ከአሕዛብ ሁሉ ለይቶ መረጣችሁ።
በፊታችሁ ተርብ ላክሁ፤ ይህም እነርሱንና ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ጭምር ከፊታችሁ አሳደደ፤ ይህ ደግሞ በራሳችሁ ሰይፍና ቀስት ያደረጋችሁት አይደለም።
እንግዲህ ሕያው አምላክ በመካከላችሁ መሆኑንና እርሱም በርግጥ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ ኤዊያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ እንዴት አድርጎ እንደሚያሳድዳቸው የምታውቁት በዚህ ነው።