መዝሙር 146:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችም አትመኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማዳን በማይችሉ በአለቆች፥ በሰው ልጅ፥ አትታመኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማዳን ስለማይችሉ በመሪዎች ወይም በማንኛውም ፍጡር አትተማመኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባቸው የቈሰለውን ይፈውሳል፥ ቍስላቸውንም ያደርቅላቸዋል። |
በዚያ ጊዜም ባለራእዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ሳይሆን በሶርያ ንጉሥ ስለ ታመንህ፣ የሶርያ ንጉሥ ሰራዊት ከእጅህ አምልጧል።
“በዚያ ቀን” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ “በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለ ካስማ ይነቀላል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ወድቆ ይከሰከሳል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።
ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፤ “ጌታችሁን እንዲህ በሉት፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች እኔን ስለ ሰደቡኝ፣ በሰማኸው ቃል አትሸበር።