መዝሙር 142:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ቀኝ ተመለከትሁ አየሁም፥ የሚያውቀኝም አጣሁ፥ መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ነፍሴም የሚያስብ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀድሞውን ዘመን ዐሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አነበብሁ፤ የእጅህንም ሥራ አነብባለሁ። |
እንደ ገና ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ አስተዋልሁም፤ የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ ኀይል በሚገፏቸው ሰዎች እጅ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም።
እነሆ፤ ሁላችሁም በየፊናችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ጊዜ አሁን ነው። እኔንም ብቻዬን ትተዉኛላችሁ፤ ይሁን እንጂ አባቴ ከእኔ ጋራ ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙላት እንዲሰበክና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳም መንጋጋ አዳነኝ።