Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 142:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤ ስለ እኔ የሚገድደው የለም፤ ማምለጫም የለኝም፤ ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 መንፈሴ በዛለ ጊዜ መንገዴን አወቅሁ፥ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በዙሪያዬ ስመለከት መሸሸጊያ የሚሆነኝ አጣሁ፤ አንድም እንኳ የሚረዳኝ ሰው አልነበረም፤ የሚጠብቀኝና የሚጠነቀቅልኝም አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሰው​ነቴ በላዬ አለ​ቀ​ች​ብኝ፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 142:4
19 Referencias Cruzadas  

አንተን ግን መልሼ ጤነኛ አደርግሃለሁ፤ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘የተናቀች ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሃልና።


ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።


ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ፣ ለጎረቤቶቼ መዘባበቻ፣ ለወዳጆቼ መሣለቂያ ሆኛለሁ፤ መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል።


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነው ነቢያት በቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩት ይፈጸም ዘንድ ነው።” በዚያ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።


የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤ እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችልም፤


ስድብ ልቤን ጐድቶታል፤ ተስፋዬም ተሟጥጧል፤ አስተዛዛኝ ፈለግሁ፤ አላገኘሁምም፤ አጽናኝም ፈለግሁ፤ አንድም አልነበረም።


በተከሰስሁበት ነገር የመጀመሪያ መከላከያዬን ሳቀርብ ማንም ሊያግዘኝ አልመጣም፤ ነገር ግን ሁሉ ትተውኝ ሄዱ። ይህንም አይቍጠርባቸው።


ዳዊት ግን በልቡ፣ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፣ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ ዐሰበ።


እረኞች የሚሸሹበት፣ የመንጋ ጠባቂዎችም የሚያመልጡበት የለም።


የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፤ ማምለጫም አያገኙም፤ ተስፋቸውም ሞት ብቻ ነው።”


እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ይጠብቃልና፤ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።


እግዚአብሔር ሆይ፤ “አንተ አምላኬ ነህ” እልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የልመና ጩኸቴን ስማ።


ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣ ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ።


ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ዝላለች፤ ልቤም በውስጤ ደንግጧል።


ሊይዙኝ ጕድጓድ ስለ ቈፈሩ፣ ለእግሮቼም በስውር ወጥመድ ስለ ዘረጉ፣ በድንገት ወራሪ ስታመጣባቸው፣ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።


“ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፣ ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios