መዝሙር 132:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለእግዚአብሔር ማለ፤ ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ እንደማለ፥ ለያዕቆብም ኀያል እንደ ተሳለ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ለአንተ የገባውን ቃል ኪዳንና ሁሉን ለምትችል ለያዕቆብ አምላክ ለአንተ እንዲህ ሲል የተሳለውን ስእለት አስታውስ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከራሱ ጀምሮ እስከ ጢሙ፥ በልብሱ መደረቢያ ላይ፥ እስከሚወርደው እስከ አሮን ጢም ድረስ እንደሚፈስ ሽቱ ነው። |
ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።
ከዚያም ንጉሥ ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞቼና ወገኖቼ ሆይ፤ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦት ማደሪያና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን ቤት ለመሥራት ዐስቤ ዕቅድ አውጥቼ ነበር።
አስጨናቂዎችሽ የራሳቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰከር ሁሉ፣ በገዛ ደማቸው ይሰክራሉ። ከዚያም የሰው ዘር ሁሉ፣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ታዳጊሽም የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ያውቃል።”
የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።