መዝሙር 128:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስትህ በቤትህ፣ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣ እንደ ወይራ ተክል ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስትህ በቤትህ እንደ ፍሬያማ የወይን ተክል ትሆናለች፤ ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ለምለም ቅርንጫፎች ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥኣን በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢአታቸውንም አበዙአት።” |
የኡላም ልጆች በቀስት መንደፍ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ እነርሱም በአጠቃላይ ቍጥራቸው አንድ መቶ ኀምሳ ወንዶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው። እነዚህ ሁሉ የብንያም ትውልዶች ነበሩ።
ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣ የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ።
እግዚአብሔር፣ የተዋበ ፍሬ ያላት፣ የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎሽ ነበር፤ አሁን ግን በታላቅ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ፣ እሳት ያነድድባታል፤ ቅርንጫፎቿ ይሰባበራሉ።
የበረሓ ከሆነው የወይራ ዛፍ የተቈረጥህና ተፈጥሮህ ወዳልሆነው ወደ መልካሙ ወይራ የገባህ ከሆንህ፣ በተፈጥሯቸው ቅርንጫፎቹ የሆኑት እነዚህ ወደ ራሳቸው ወይራ ዛፍ መግባታቸውማ ምን ያህል ይሆን?