መዝሙር 112:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፥ መሓሪ፥ ርኅሩኅና ጻድቅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሕረትና ቸርነት፥ ቅንነትም ለሚያደርግ ለደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው። |
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።
ይህ ከሆነ ብርሃንህ እንደ ንጋት ጮራ ይፈነጥቃል፤ ፈውስህ ፈጥኖ ይደርሳል፤ ጽድቅህ ቀድሞህ ይሄዳል፤ የእግዚአብሔር ክብር ደጀን ይሆንልሃል።
የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፤ ጽድቅን የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።