ምሳሌ 7:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቼ ሆይ፤ አሁንም አድምጡኝ፤ የምለውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቼ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስሙኝ የአፌንም ቃል አድምጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ የምልህንም በጥንቃቄ ስማ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስማኝ፥ ወደ አፌ ቃል አድምጥ። |
ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።