ምሳሌ 7:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፥ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወት እንድትኖር ትእዛዞቼን ጠብቅ፤ የማስተምርህንም ሁሉ እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አክብረው ትጸናለህም። ከእርሱ በቀር ሌላውን አትፍራ፥ ከእርሱ በቀር የሚገድልህም የሚያድንህም የለምና። ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤ ቃሌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤ |
ጆሯችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ። ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “አሳልፈው አይሰጡህም፤ ብቻ የምነግርህን የእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ፤ መልካም ይሆንልሃል፤ ሕይወትህም ትተርፋለች።