ምሳሌ 4:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ ስትሮጥም አትደናቀፍም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይታገድም፥ ብትሮጥም አትሰናከልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥበብ ብትራመድ እርምጃህ አይታገድም፤ ብትሮጥም አትሰናከልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤ በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም። |
እያለቀሱ ይመጣሉ፤ እያጽናናሁ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ ኤፍሬም በኵር ልጄ ነውና፣ በውሃ ምንጭ ዳር፣ በማይሰናከሉበት ቀና መንገድ እመራቸዋለሁ።