36 ከሥሬ ያለውን ስፍራ ለአረማመዴ አሰፋህልኝ፤ እግሬም አልተንሸራተተም።
36 ለደኅንነቴም ጋሻን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም አሳደገችኝ፥
36 መረማመጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ ስትሮጥም አትደናቀፍም።
ርምጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተሰነካከሉም።
የጽድቄ አምላክ ሆይ፤ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።
“አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣ ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣ ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል።
ነገር ግን የምጠመቀው ጥምቀት አለኝ፤ እስኪፈጸምም ድረስ እንዴት ተጨንቄአለሁ?
የርምጃው ብርታት ይደክማል፤ የገዛ ዕቅዱም ይጥለዋል።
ነፍሴን ለማጥፋት የሚሹ ግን፣ ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።