ምሳሌ 26:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በረዶ በበጋ፣ ዝናብ በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ፣ ክብርም ለሞኝ አይገባውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በረዶ በበጋ ዝናብም በመከር እንደማይፈልግ ሁሉ፥ እንዲሁም ለሞኝ ክብር አይገባውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረዶ በበጋ ወራት፥ ዝናብም በመከር ወራት እንደማያስፈልግ ሁሉ ለሞኝ ክብር አይገባውም። |
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ትውጣና እናንተን፣ የሴኬምንና የቤት ሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፣ ከሴኬምና ከቤት ሚሎን ገዦች ትውጣና አቢሜሌክን ትብላ።”
ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፣ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምፁን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ “የሴኬም ገዦች ሆይ፤ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ።