ዘኍል 34:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፋፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ምድሪቱን በሕዝቡ መካከል ያከፋፍሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ። |
ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል የየነገዱ ጐሣ አባቶች የደለደሉላቸው፣ እስራኤላውያንም በከነዓን ምድር የወረሱት ርስት ይህ ነው።
እንግዲህ ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የየጐሣ መሪዎች ሴሎ ላይ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ ያደላደሉት ርስት ይህ ነው፤ የምድሪቱንም አከፋፈል በዚህ ሁኔታ ፈጸሙ።