Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 13:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሙሴም እንደ ጌታ ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ከእስራኤል መሪዎች መካከል ከፋራን ምድረ በዳ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ላከ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከፋ​ራን ምድረ በዳ ላካ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 13:3
11 Referencias Cruzadas  

ከዚያም እስራኤላውያን ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው ደመናው በፋራን ምድረ በዳ እስኪያርፍ ድረስ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ ተጓዙ።


ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ከሐጼሮት ተነሣ፤ በፋራን ምድረ በዳም ሰፈረ።


“ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።”


ሰዎቹም፣ ሙሴና አሮን መላውም የእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረ በዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ ተመለሱ፤ ያዩትንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ አስረዱ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።


ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ ከሮቤል ነገድ፣ የዛኩር ልጅ ሳሙኤል፤


አባቶቻችሁ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ከቃዴስ በርኔ በላክኋቸው ጊዜም ያደረጉት ይህንኑ ነበር።


“ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፤


ከዚያም አምላካችን እግዚአብሔር ባዘዘን መሠረት ከኮሬብ ተነሥተን እንዳያችሁት በዚያ ጭልጥ ባለና በሚያስፈራ ምድረ በዳ ዐልፈን፣ በኰረብታማው በአሞራውያን አገር በኩል ወደ ቃዴስ በርኔ መጣን።


ይህም ሐሳብ መልካም መስሎ ታየኝ፤ እኔም ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሰው በማድረግ ከእናንተ ዐሥራ ሁለት ሰዎች መረጥሁ።


እግዚአብሔር ከቃዴስ በርኔ ባስወጣችሁ ጊዜ፣ “ውጡ፤ የሰጠኋችሁንም ምድር ርስት አድርጋችሁ ውረሷት” አላችሁ። እናንተ ግን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፤ እርሱን አልታመናችሁበትም፤ አልታዘዛችሁትምም።


ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ አርማቴም ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos