በኢየሩሳሌም ተቀምጦ እንዳይገዛም ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ቦታ አሰረው፤ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት።
ዘኍል 34:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወሰኑም ከሴፋማ አንሥቶ ከዓይን በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ሪብላ ቍልቍል ይወርድና ከኪኔሬት ባሕር በስተምሥራቅ እስካሉት ሸንተረሮች ድረስ ይዘልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ከሴፋማ በዐይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ ሪብላ ይወርዳል፤ እስከ ኪኔሬት የባሕር ወሽመጥ በምሥራቅ በኩል ይደርሳል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወሰኑም ከሴፋም ተነሥቶ ከዓይን በስተምሥራቅ በኩል ወደ ሪብላ ይቀጥልና በገሊላ ባሕር በስተ ምሥራቅ ወዳሉት ኮረብታዎች ይደርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳርቻውም ከሴፋማ በዐይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ አርቤላ ይወርዳል፤ እስከ ኬኔሬት የባሕር ወሽመጥ በምሥራቅ በኩል ይደርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳርቻውም ከሴፋማ በዓይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ ሪብላ ይወርዳል፤ እስከ ኪኔሬት የባሕር ወሽመጥ በምሥራቅ በኩል ይደርሳል፤ |
በኢየሩሳሌም ተቀምጦ እንዳይገዛም ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ቦታ አሰረው፤ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት።
ከዚያም ወሰኑ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ መጨረሻው የጨው ባሕር ይሆናል። “ ‘እንግዲህ በዙሪያዋ ካሉት ወሰኖቿ ጋራ ምድራችሁ ይህች ናት።’ ”
የምዕራቡ ወሰን፣ በዓረባ የሚገኘው ዮርዳኖስ ሲሆን፣ ይኸውም ከፈስጋ ተረተሮች በታች፣ ከኪኔሬት አንሥቶ የጨው ባሕር እስከሚባለው እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ነው።
እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕር እስከ ጨው ባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤትየሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቷል።
በሸለቆው ውስጥ ደግሞ ቤትሀራምን፣ ቤትኒምራን፣ ሱኮትን፣ ዳፎንንና እስከ ኪኔሬት ባሕር ጫፍ የሚደርሰውን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ቀሪውን የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት ያካትታል።