La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 31:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ላይ፣ ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከየዐምሳው ሰውና እንስሳ አንዳንድ መርጦ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጣቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከኀምሳ አንድ ወሰደ፥ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው የጌታን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም ድርሻ ሙሴ ከኀምሳው አንድ እስረኛ፥ ከኀምሳው አንድ እንስሳ ወስዶ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር ድንኳን ላይ ኀላፊነት ላላቸው ለሌዋውያን ሰጠ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ድርሻ ከሰ​ውና ከእ​ን​ስሳ ከሃ​ምሳ አንድ ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ሥር​ዐት ለሚ​ጠ​ብቁ ሌዋ​ው​ያን ሰጠ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከአምሳ አንድ ወሰደ፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ።

Ver Capítulo



ዘኍል 31:47
12 Referencias Cruzadas  

እናንተ በሌሊት ቆማችሁ በእግዚአብሔር ቤት የምታገለግሉ፣ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ እግዚአብሔርን ባርኩ።


እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።


ሌዋውያን ግን በእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ድንኳኖቻቸውን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፤ የምስክሩ ማደሪያ ድንኳን ኀላፊዎች ሌዋውያን ናቸው።”


ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ደግሞ ከሰውም ይሁን ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ፣ ከፍየል ወይም ከሌሎች እንስሳት ከየዐምሳው አንዳንድ መርጠህ፣ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ስጣቸው።”


ዐሥራ ስድስት ሺሕ ሰው።


ከዚያም በኋላ በሰራዊቱ ክፍሎች ላይ የተሾሙት የሻለቆችና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ ቀርበው፣


በዚያችም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር ለሆነው መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ ዕንጨት ቈራጮችና ውሃ ቀጂዎች አደረጋቸው።