ዘኍል 30:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት በሚሳልበት ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሱን ግዴታ ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ ቃሉን ሳያጥፍ ያለውን ሁሉ መፈጸም አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ለጌታ ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አያፍርስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት ቢሳል ወይም ከአንድ ነገር ራሱን ለመከልከል በመሐላ ቃል ቢገባ፥ አደርጋለሁ ያለውን ሁሉ መፈጸም አለበት እንጂ የሰጠውን የተስፋ ቃል ማስቀረት አይገባውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም መሐላን ቢምል፤ ራሱንም ቢለይ፥ ቃሉን አያርክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አይስበር፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ። |
እነሆ፤ የምሥራች የሚያመጣው፣ ሰላምን የሚያውጀው ሰው እግር፣ በተራሮች ላይ ነው፤ ይሁዳ ሆይ፤ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ምናምንቴ ሰዎች አይወርሩህም፤ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።
“እናንተ ዕውር መሪዎች፤ ወዮላችሁ! ‘ማንም በቤተ መቅደስ ቢምል ምንም አይደለም፤ ነገር ግን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል መሐላው ይደርስበታል’ ትላላችሁ።
ስለዚህ ዕሺ አትበላቸው፤ ምክንያቱም ከመካከላቸው ከአርባ በላይ የሚሆኑት ሊገድሉት አድፍጠው እየጠበቁት ነው፤ ደግሞም እስኪገድሉት ድረስ እህል ውሃ ላለመቅመስ ተማምለዋል፤ አሁንም ተዘጋጅተው የአንተን መልስ እየተጠባበቁ ነው።”
ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ አለቆች ጋራ ሄደ፤ ሕዝቡም በላያቸው ላይ አለቃና አዛዥ አደረጉት፤ ዮፍታሔም የተናገረውን ቃል ሁሉ ምጽጳ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ደገመው።