ዘኍል 29:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ጌታ እርሱን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ነገራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው። |
“ ‘ከስእለትና ከበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቍርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቍርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በበዓላታችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።’ ”