የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው።
ዘኍል 28:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እንዲህ በላቸው፤ ‘በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት መሥዋዕት ይህ ነው፤ አንድ ዓመት የሆናቸውንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በየዕለቱ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእኔ የሚቀርበውም በእሳት የሚቃጠል የምግብ ቊርባን የሚከተለው ነው፦ በየቀኑ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላቸውና ምንም ነውር የሌለባቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች ይሁኑ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በላቸው፦ በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በላቸው፦ በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። |
የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው።
ሙሴ ስለ መሥዋዕት አቀራረብ ባዘዘው መሠረት በእያንዳንዱ የበዓል ቀን ይኸውም በየሰንበቱ፣ በየወሩ መባቻና በሦስቱ የዓመት በዓላት ማለትም በቂጣ በዓል፣ በሰባቱ ሱባዔ የመከር በዓልና በዳስ በዓል ጊዜ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ።
ከዚያም በኋላ መደበኛውን የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የወር መባቻን መሥዋዕት፣ በተቀደሱት የእግዚአብሔር በዓላት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
“የጦር ሰራዊቱም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ።
ከሰማይ ሰራዊት አለቃ ጋራ እስኪተካከል ድረስ ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ የልዑሉንም የዘወትር መሥዋዕት ወሰደበት፤ የመቅደሱንም ስፍራ አረከሰ።
ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላውም ቅዱስ እንዲህ አለው፤ “ስለ ዘወትሩ መሥዋዕት፣ ለጥፋት ምክንያት ስለ ሆነው ዐመፅ፣ ከእግር በታች እንዲረገጡ ዐልፈው ስለሚሰጡት መቅደስና ሰራዊት የታየው ራእይ የሚፈጸመው መቼ ነው?”
የአሮንም ልጆች በመሠዊያው በሚነድደው ዕንጨት ላይ ባለው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አድርገው ያቃጥሉት፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።
“አሮንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ስለሚቃጠለው መሥዋዕት አቀራረብ የምትከተለው ሥርዐት ይህ ነው፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት ሌሊቱን ሁሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጥ፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ሲነድድ ይደር።
“ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤ ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤ በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣ በየሦስቱ ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።
በዚህም ዐይነት ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሆኖ በየዕለቱ ለሰባት ቀን በእሳት ለሚቀርብ መሥዋዕት የምግብ ቍርባን አዘጋጁ፤ ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋራ ሆኖ በተጨማሪ ይቀርባል።
ከእህል ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በተጨማሪ፣ እነዚህን ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋራ አቅርቡ። እንስሳቱም እንከን የሌላቸው መሆናቸውን አረጋግጡ።
ማስተስረያ እንዲሆንም ለኀጢአት መሥዋዕት ከሚቀርበው እንዲሁም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ቀርቦ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋራ በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው።