ዘኍል 27:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሰለጰዓድ ልጆች ትክክለኛ ነገር ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ወደ እነርሱ ይተላለፍ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች የጠየቁት ትክክል ነገር ነው፤ ስለዚህ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ርስት ስጣቸው፤ የአባታቸው ድርሻ ወደ እነርሱ ይተላለፍ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ ስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ አሳልፈህ ስጥ። |
እንግዲህ የሰለጰዓድን ሴት ልጆች በተመለከተ እግዚአብሔር የሚያዝዘው ይህ ነው፤ ከአባታቸው ነገድ ወገን እስከ ሆነ ድረስ የወደዱትን ማግባት ይችላሉ።
እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ መሪዎቹ ቀርበው፣ “ከወንድሞቻችን ጋራ ርስት እንድንካፈል እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞታል” አሏቸው። ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከአባታቸው ወንድሞች ጋራ ርስት ሰጣቸው።