ዘኍል 26:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤ በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የስምዖን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የስምዖን ነገድ ተወላጆች፦ ነሙኤል፥ ያሚንና፥ ያኪን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የስምዖንም ልጆች በየወገናቸው፤ ከናሙሄል የናሙሄላውያን ወገን፥ ከኢያሚን የኢያሚናውያን ልጆች ወገን፥ ከያክን የያክናውያን ልጆች ወገን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የስምዖን ልጆች በየወገናቸው ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን፥ |
የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው።
የስምዖን ወንዶች ልጆች፣ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና የከነዓናዊቱም ልጅ ሳኡል ነበሩ። እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው።
ከስምዖን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።