ዘኍል 26:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት መቶ ዐምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከርሱ ጋራ ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያም ወገን በሞተ ጊዜ፥ እሳቲቱም ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች ባቃጠለች ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ እነርሱን ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም ምድር ተከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም በሞቱ ጊዜ እሳት ወርዶ ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች አቃጠላቸው፤ ለሕዝቡም መቀጣጫ ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኅበሩም በሞቱ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ወገን በሞተ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ። |
በእነርሱ ላይ ከደረሰው የተነሣ በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ፣ ‘እግዚአብሔር፣ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግብህ’ ብለው ይራገማሉ፤
ፊቴን በክፋት ወደዚያ ሰው እመልሳለሁ፤ መቀጣጫና መተረቻ አደርገዋለሁ፤ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ሙሴን ተቃወሙት። ከእነዚህም ጋራ ታዋቂ የማኅበረ ሰቡ መሪዎች የሆኑና በጉባኤ አባልነት የተመረጡ ሁለት መቶ ዐምሳ እስራኤላውያን ዐብረው ነበሩ።
እነዚህም ሕይወታቸውን ለማጥፋት ኀጢአት የሠሩ ሰዎች ጥና ናቸው፤ ጥናዎቹም በእግዚአብሔር ፊት የቀረቡና የተቀደሱ በመሆናቸው ለመሠዊያው መለበጫ እንዲሆኑ ቀጥቅጠህ አሣሣቸው፤ እነዚህም ለእስራኤላውያን ማስጠንቀቂያ ይሁኑ።”
“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋራ አልነበረም፤ የሞተው ግን በራሱ ኀጢአት ሲሆን፣ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም።
የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንና አቤሮንን ከነቤተ ሰቦቻቸው፣ ከነድንኳናቸውና ከነእንስሳታቸው በመላው እስራኤል መካከል ምድር እንዴት አፏን ከፍታ እንደ ዋጠቻቸው እነርሱ አላዩም።
እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ፣ በዙሪያቸውም ያሉ ከተሞች ለሴሰኛነትና ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጭ ለሆነ ሩካቤ ሥጋ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤ እነርሱም በዘላለም እሳት በመቀጣት ለሚሠቃዩት ምሳሌ ሆነዋል።