Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 26:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የኤልያብም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን ናቸው፤ እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ቆሬን ከተከተሉት ሰዎች ጋር በመሆን በጌታ ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተገዳደሩ ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የኤሊአብ ልጆች ነሙኤል፥ ዳታንና አቤሮን ነበሩ፤ ዳታንና አቤሮንም በማኅበሩ ተመርጠው የነበሩት ሲሆኑ እነርሱም ከቆሬና ከተከታዮቹ ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተፈታተኑአቸው ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የኤ​ል​ያ​ብም ልጆች፥ ናሙ​ኤል፥ ዳታን፥ አቤ​ሮን፤ እነ​ዚ​ህም ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተጣሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የኤልያብም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን፤ እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን ተጣሉ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 26:9
5 Referencias Cruzadas  

ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች።


እነዚህ ከማኅበረ ሰቡ የተመረጡ የየነገዱ አለቆች ሲሆኑ እነርሱም የእስራኤል ጐሣዎች መሪዎች ነበሩ።


የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣


ወዮላቸው! በቃየን መንገድ ሄደዋል፤ ለገንዘብ ሲስገበገቡ በበለዓም ስሕተት ውስጥ ወድቀዋል፤ በቆሬም ዐመፅ ጠፍተዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos