ዘኍል 21:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስትን ወረወርንባቸው፤ ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ፤ እሳቱ እስከ ሜድባ እስኪዛመት ድረስ ደመሰስናቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዘሮቻቸው ተደመሰሱ ከሐሴቦን እስከ ዲቦን፥ እሳቱ እስከ ሜዴባ እስኪስፋፋ ድረስ አጠፋናቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘራቸውም ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፋ፤ ሴቶቻቸውም ደግሞ በሞዓብ ላይ እሳትን አነደዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገተርናቸው፤ ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ፤ ኖፋም እስኪደርሱ እስከ ሜድባ አፈረስናቸው። |
ከዚያም ባለፍላጻዎቹ ከግንቡ ላይ ሆነው በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ ቀስት ስለ ለቀቁ፣ ከንጉሡ አገልጋዮች ጥቂቶቹን ገደሉ፤ አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ።”
ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺሕ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤ እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣ አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።
ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
የዲሞን ወንዞች በደም ተሞልተዋል፤ በዲሞን ላይ ግን ከዚያ ነገር የበለጠ አመጣለሁ፤ ከሞዓብ በሚሸሹት፣ በምድሪቱም ላይ በሚቀሩት አንበሳ እሰድዳለሁ።
“ሞዓብን የሚያጠፋ፣ በአንቺ ላይ ይመጣልና፤ የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤ አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከክብርሽ ውረጂ፤ በደረቅም መሬት ተቀመጪ።
ይህም ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔርና በሸለቆው መካከል ካለችው ከተማ አንሥቶ እስከ ዲቦን የሚደርሰውን የሜድባን ደጋማ ምድር በሙሉ ይይዛል፤