ዘኍል 21:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደተባለው የውሃ ጕድጓድ ጕዟቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም ጌታ ሙሴን፦ “ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ የተናገረለት ጉድጓድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ተነሥተው “የውሃ ጒድጓዶች” ወደ ተባለው ስፍራ ሄዱ፤ በእዚያም እግዚአብሔር ሙሴን “ሕዝቡን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፥ “ሕዝቡን ሰብስብ፤ የሚጠጡት ውኃ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ ወደ ተናገረላት ጕድጓድ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን፦ ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረለት ጕድጓድ ነው። |
ኮሬብ አጠገብ ባለው ዐለት በዚያ እኔ በአንተ ፊት እቆማለሁ። ዐለቱን ምታው፤ ከርሱም ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ ይወጣል።” ስለዚህ ሙሴ በእስራኤል አለቆች ፊት ይህንኑ አደረገ።
“በትሪቱን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን በአንድነት ሰብስቡ፤ እነርሱም እያዩ ዐለቱን ተናገሩት፤ ዐለቱም ውሃ ያወጣል። አንተም ለማኅበረ ሰቡ ከዐለቱ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እነርሱና ከብቶቻቸውም ይጠጣሉ።”
ኢየሱስም፣ “የእግዚአብሔርን ስጦታ ብታውቂና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑን ብትረጂ ኖሮ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም የሕይወትን ውሃ በሰጠሽ ነበር” ሲል መለሰላት።