ዘኍል 20:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በትሪቱን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን በአንድነት ሰብስቡ፤ እነርሱም እያዩ ዐለቱን ተናገሩት፤ ዐለቱም ውሃ ያወጣል። አንተም ለማኅበረ ሰቡ ከዐለቱ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እነርሱና ከብቶቻቸውም ይጠጣሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ እነርሱም ዓይናቸው እያየ ድንጋዩ ውኃን እንዲሰጥ ተናገሩት፤ ለእነርሱም ከድንጋዩ ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ለማኅበሩና ለከብቶቻቸው የሚጠጣ ወኃ ትሰጣቸዋለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን በትር ወስደህ አንተና አሮን ሆናችሁ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰብስቡ፤ እዚያም በእነርሱ ሁሉ ፊት ሆነህ ያንን አለት ውሃውን እንዲያወጣ እዘዘው፤ በዚህ ዐይነት ከአለቱ ውስጥ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም እነርሱና እንስሶቻቸውም ጠጥተው ይረካሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህችን በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበሩን ሰብስቡ፤ ዐለቷንም በፊታቸው እዘዟት፤ ውኃ ትሰጣለች፤ ከድንጋይዋም ውኃ ታወጡላቸዋላችሁ፤ እንዲሁም ማኅበሩን፥ ከብቶቻቸውንም ታጠጡላቸዋላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት፤ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ። |
በተራቡ ጊዜ ከሰማይ መና ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ከዐለት ውሃ አፈለቅህላቸው፤ ልትሰጣቸው በተዘረጋች እጅ ወደማልህላቸውም ምድር ገብተው እንዲወርሱ አዘዝሃቸው።
ሙሴም ኢያሱን፣ “ከሰዎቻችን አንዳንዶቹን ምረጥና አማሌቃውያንን ለመውጋት ውጣ፤ በነገው ዕለት የእግዚአብሔርን በትር በእጆቼ ይዤ በኰረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ።”
ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንደ አዘዛቸው አደረጉ። እርሱም በፈርዖንና በሹማምቱ ፊት በትሩን አንሥቶ የአባይን ወንዝ ውሃ መታ፤ ውሃውም በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ።
ልዑላን ለቈፈሩት፣ የሕዝብ አለቆች በበትረ መንግሥታቸውና በበትሮቻቸው ላጐደጐዱት፣ የውሃ ጕድጓድ ዘምሩለት።” ከዚህ በኋላ ከምድረ በዳው ወደ መቴና ሄዱ፤
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩ፣ በበለሷ ዛፍ ላይ የሆነውን ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ይህን ተራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት እንኳ ይሆናል፤
እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ በሰማይ ያለው አባት ታዲያ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጥ?”
መለከቱ ሲነፋ ሕዝቡ ጮኸ፤ የመለከቱ ድምፅ ተሰምቶ፣ ሕዝቡ በኀይል ሲጮኽ ቅጥሩ ፈረሰ፤ እያንዳንዱም ሰው ሰተት ብሎ ገባ፤ ከተማዪቱም በእጃቸው ወደቀች።
የማያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በምትሰሙበት ጊዜ፣ ሕዝቡ ሁሉ ከፍ ያለ ጩኸት ያሰማ፤ ከዚያም የከተማዪቱ ቅጥር ይፈርሳል፤ ሕዝቡም ወደ ላይ ይወጣል፤ እያንዳንዱም ሰው በቀጥታ ይገባል።”