እስራኤላውያንም መልሰው፣ “አውራውን መንገድ ይዘን እንሄዳለን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን የትኛውንም ውሃችሁን ከጠጣን ዋጋውን እንከፍላለን፤ በእግር ዐልፈን መሄድ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አንፈልግም።” አሏቸው።
ዘኍል 20:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤዶም ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በዚህ በኩል አታልፉም፤ እናልፋለን የምትሉ ከሆነ በሰልፍ ወጥተን በሰይፍ እንመታችኋለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤዶምያስም፦ “በምድሬ ላይ አታልፍም አለበለዚያ ግን አንተን በሰይፍ ልገጥምህ እወጣለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤዶማውያን ግን እንዲህ አሉ፤ “በአገራችን አልፋችሁ እንድትሄዱ አንፈቅድላችሁም! ለመግባት ብትሞክሩ ግን በሰልፍ ወጥተን እንወጋችኋለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤዶምያስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታልፍም፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዋጋለን፤ በጦርም እቀበልህ ዘንድ እወጣለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤዶምያስም፦ በሰይፍ እንዳልገጥምህ በምድሬ ላይ አታልፍም አለው። |
እስራኤላውያንም መልሰው፣ “አውራውን መንገድ ይዘን እንሄዳለን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን የትኛውንም ውሃችሁን ከጠጣን ዋጋውን እንከፍላለን፤ በእግር ዐልፈን መሄድ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አንፈልግም።” አሏቸው።
ሴዎን ግን እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዲያልፍ አልፈቀደም፤ ሰራዊቱን በሙሉ አሰባስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ወጣ፤ ያሀጽ እንደ ደረሰም ከእስራኤል ጋራ ጦርነት ገጠመ።
እስራኤላውያን በኤዶም ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመንገድ ሳለ ትዕግሥቱ ዐለቀ፤
በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ ሞዓባውያን እንዳደረጉልን ሁሉ፣ አንተም አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክንሻገር ድረስ እንደዚሁ አድርግልን።”