አሁንም እንደ ገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት “ከእንግዲህ ባሌ ያቀርበኛል” አለች፤ ስለዚህ ሌዊ ብላ ጠራችው።
ዘኍል 18:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ዐብረዋችሁ እንዲሆኑና እንዲረዷችሁ ከአባትህ ነገድ ሌዋውያንን አምጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ሳላችሁ ከአንተ ጋር በአንድነት እንዲሆኑ፥ እንዲያገለግሉህም፥ የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ደግሞ ከአንተ ጋር አምጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ከእናንተ ጋር በመሥራት ይረዱአችሁ ዘንድ፥ የሌዊ ነገድ የሆኑትን ወገኖችህን ውሰድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ወደ አንተ ሰብስብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት ይሁኑ፤ ያገልግሉህም፤ አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ከአንተ ጋር አቅርብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ያገልግሉህም፤ አንተ ግን ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ። |
አሁንም እንደ ገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት “ከእንግዲህ ባሌ ያቀርበኛል” አለች፤ ስለዚህ ሌዊ ብላ ጠራችው።
የቤተ መቅደሱ በር ኀላፊ በመሆንና በርሱም ውስጥ በማገልገል፣ መቅደሴን ሊያገለግሉ ይችላሉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዐርደው ስለ ሕዝቡ ሊሠዉ፣ በፊታቸው ሊቆሙና ሊያገለግሏቸው ይችላሉ።
“ ‘ነገር ግን እስራኤላውያን ከመንገዴ ስተው በወጡ ጊዜ፣ የመቅደሴን ሥራ በታማኝነት ያከናወኑት የሳዶቅ ዘር የሆኑት ሌዋውያን ካህናት፣ በፊቴ ቀርበው ያገለግሉኛል፤ በፊቴ ቆመው የሥብና የደም መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሌዋውያን ግን በእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ድንኳኖቻቸውን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፤ የምስክሩ ማደሪያ ድንኳን ኀላፊዎች ሌዋውያን ናቸው።”
ይህን ያደረገውም፣ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት ነው፤ ይህም ከአሮን ዘር በቀር ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ዕጣን እንዳያጥን አለዚያ ግን፣ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ እንደሚሆን ለእስራኤላውያን የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነበር።
እነርሱም የመገናኛውን ድንኳን ለመከባከብ ማለትም በድንኳኑ ውስጥ የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ኀላፊነት በመውሰድ ዐብረዋችሁ ይሁኑ፤ ከዚህ በተረፈ ግን እናንተ ወዳላችሁበት ማንም ሰው አይጠጋ።
“አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና ዕቃዎቹን፣ ንዋየ ቅድሳቱንም በሙሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ሲሆን፣ ቀዓታውያን ለመሸከም ይምጡ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን መንካት የለባቸውም፤ ስለዚህ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያሉትን እነዚህን ዕቃዎች የሚሸከሙ ቀዓታውያን ናቸው።
እስራኤላውያንን ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት እንዲያከናውኑና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ ቢቀርቡ እንዳይቀሠፉ ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፣ ከእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ሌዋውያኑን ስጦታ አድርጌ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።”
ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር ሆነው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት ለማከናወን ገቡ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አስፈላጊውን በሌዋውያኑ አደረጉ።