የእግዚአብሔርም ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ተገናኝተው ልጆች በወለዱ ጊዜም ሆነ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንቱ ዘመን በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ ናቸው።
ዘኍል 16:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴን ተቃወሙት። ከእነዚህም ጋራ ታዋቂ የማኅበረ ሰቡ መሪዎች የሆኑና በጉባኤ አባልነት የተመረጡ ሁለት መቶ ዐምሳ እስራኤላውያን ዐብረው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች የሆኑ ከጉባኤው የተመረጡ፥ በዝናቸውም የገነኑ የማኅበሩ አለቆች ጋር በመሆን እነርሱ በሙሴ ላይ ተነሡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ጋር በእስራኤላውያን ዘንድ ዝናቸው የታወቀና ለሕዝብ መሪነት የተመረጡ ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎችን ወስደው በሙሴ ላይ ተነሡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሙሴም ላይ ተነሡ፤ ከእስራኤልም ልጆች በምክር የተመረጡ፥ ዝናቸውም የተሰማ ሁለት መቶ አምሳ የማኅበሩ አለቆች ከእነርሱ ጋር ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፤ ከጉባኤው የተመረጡ ዝናቸውም የተሰማ የማኅበሩ አለቆች ነበሩ። |
የእግዚአብሔርም ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ተገናኝተው ልጆች በወለዱ ጊዜም ሆነ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንቱ ዘመን በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ ናቸው።
የየቤተ ሰቡም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፤ ይሽዒ፣ ኤሊኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤርምያ፣ ሆዳይዋ፣ ኢየድኤል፤ እነዚህ ጀግና ተዋጊዎች፣ የታወቁ ሰዎችና የየቤተ ሰባቸው አለቆች ነበሩ።
እነርሱም ዕርቃን አስቀሯት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ነጠቋት፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሏት፤ በሴቶችም ዘንድ መተረቻ ሆና ቀረች፤ ፍርድም ተፈጸመባት።
የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።
“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋራ አልነበረም፤ የሞተው ግን በራሱ ኀጢአት ሲሆን፣ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም።