ዘኍል 14:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካለማመናችሁ የተነሣ ከእናንተ የመጨረሻው በድን እዚሁ ምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ፣ ልጆቻችሁ መከራ እየበሉ አርባ ዓመት እረኞች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት እረኛች ይሆናሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ዝሙታችሁን ይሸከማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቻችሁም በእናንተ አለማመን ምክንያት ከእናንተ የመጨረሻው በድን በምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ አርባ ዓመት ሙሉ ጽኑ መከራ እየተቀበሉ በዚህ ምድረ በዳ ይንከራተታሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅበዘበዛሉ፤ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ግልሙትናችሁን ይሸከማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅበዘበዛሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ግልሙትናችሁን ይሸከማሉ። |
አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤
እስራኤል ሆይ፤ ደስ አይበልሽ፤ እንደ ሌሎችም ሕዝቦች ሐሤት አታድርጊ፤ በአምላክሽ ላይ አመንዝረሻልና፤ በየእህል ዐውድማውም ላይ፣ ለጋለሞታ የሚከፈለውን ዋጋ ወድደሻል።
የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ስለ ነደደ፣ በፊቱ ክፉ ነገር ያደረገው ያ ትውልድ በሙሉ እስኪያልቅ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው።
በእግዚአብሔር ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።
በአርባኛው ዓመት፣ በዐሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን እስራኤላውያንን በሚመለከት እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ሙሴ ለእነርሱ ነገራቸው።
ቃዴስ በርኔን ከለቀቅንበት ጊዜ አንሥቶ የዘሬድን ደረቅ ወንዝ እስከ ተሻገርንበት ጊዜ ድረስ ሠላሳ ስምንት ዓመት ዐለፈ። በዚያ ጊዜም ለጦርነት ብቁ የሆኑት የዚያ ትውልድ ወንዶች ሁሉ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ አስቀድሞ በማለው መሠረት ከሰፈሩ ፈጽመው ዐለቁ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ባርኳችኋል፤ በዚህ ጭልጥ ባለው ምድረ በዳ ባደረጋችሁት ጕዞ ጠብቋችኋል። በእነዚህ አርባ ዓመታት አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ነበርና አንዳችም ነገር አላጣችሁም።
አምላክህ እግዚአብሔር ትእዛዞቹን መጠበቅህንና በልብህ ያለውን ለማወቅ፣ ትሑት ሊያደርግህና ሊፈትንህ በእነዚህ አርባ ዓመታት በዚህ ምድረ በዳ ጕዞህ ሁሉ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።
“አሁንም እነሆ፤ ልክ እግዚአብሔር እንዳለው ይህን ለሙሴ ከተናገረበት ጊዜ አንሥቶ እስራኤል በምድረ በዳ ሲንከራተት እኔን አርባ ዐምስት ዓመት በሕይወት ጠብቆ አኑሮኛል፤ ይኸው ዛሬ ሰማንያ ዐምስት ዓመት ሆነኝ።
ግብጽን ለቅቀው በወጡ ጊዜ መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙ፣ እነርሱ ሞተው እስኪያልቁ ድረስ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይንከራተቱ ነበር። እግዚአብሔር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው ቃል የገባላቸውን ያችን ማርና ወተት የምታፈስስ ምድር እንደማያዩአት ምሏልና።