ዘኍል 12:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ከሐጼሮት ተነሣ፤ በፋራን ምድረ በዳም ሰፈረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ከሐጼሮት ተጓዙ፥ በፋራንም ምድረ በዳ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ከሐጼሮት ተነሥተው በፋራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ከአሴሮት ተጓዙ፤ በፋራንም ምድረ በዳ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ከሐጼሮት ተጓዙ፥ በፋራንም ምድረ በዳ ሰፈሩ። |
ሰዎቹም፣ ሙሴና አሮን መላውም የእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረ በዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ ተመለሱ፤ ያዩትንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ አስረዱ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።