ዘኍል 1:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌዊ ነገድ ቤተ ሰቦች ግን ከሌሎች ጋራ ዐብረው አልተቈጠሩም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሌዋውያን ግን በየአባቶቻቸው ነገድ ከእነርሱ ጋር አልተቈጠሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያን ግን ከሌሎች ነገዶች ጋር አብረው አልተቈጠሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያን ግን በየአባቶቻቸው ነገድ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያን ግን በየአባቶቻቸው ነገድ ከእነርሱ ጋር አልተቈጠሩም። |
በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በምስክሩ ማደሪያ፣ በውስጡ ባሉት በመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ እንዲሁም ከዚሁ ጋራ በተያያዙ በማናቸውም ነገሮች ላይ ኀላፊዎች ይሁኑ፤ ማደሪያውንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ይሸከሙ፤ በውስጡ ያገልግሉ፤ ድንኳናቸውንም በዙሪያው ይትከሉ።
እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ በየአገልግሎቱና በየሸክም ሥራው ተደለደለ። ስለዚህም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ቈጠራቸው።