Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 3:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ባነጋገረው ጊዜ የአሮንና የሙሴ ትውልድ ይህ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታም በሲና ተራራ ላይ ሙሴን በተናገረበት ቀን የአሮንና የሙሴ ትውልድ ይህ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ባነጋገረው ጊዜ የአሮንና የሙሴ ትውልድ ይህ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ሙሴን በተ​ና​ገ​ረ​በት ቀን የአ​ሮ​ንና የሙሴ ትው​ልድ ይህ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም በሲና ተራራ ላይ ሙሴን በተናገረበት ቀን የአሮንና የሙሴ ትውልድ ይህ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 3:1
11 Referencias Cruzadas  

እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።


የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው።


እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የሰጣቸው ትእዛዞች እነዚህ ናቸው።


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ አለው፤


ስለ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት፣ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ሙሴና አሮን ነበሩ።


በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።


የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።


የተጻፈው የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፤


እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር፣


ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios