ከዚያም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የእስራኤልን ነገድ አለቆችና የእስራኤልን ጐሣዎች ሹማምት ሁሉ፣ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ዘኍል 1:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከየነገዱ የአባቶች ቤት ተጠሪ የሆነ አንድ ሰው ከእናንተ ጋራ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከየነገዱም አንድ ሰው የአባቶቹ ቤት አለቃ የሆነ ከእናንተ ጋር ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ የቤተሰብ አለቃ ከእናንተ ጋር ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ እየአባቶቻቸው ቤት ከየነገዱ አለቆች አንድ አንድ ሰው ከእናንተ ጋር ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከየነገዱም አንድ ሰው የአባቶቹ ቤት አለቃ ከእናንተ ጋር ይሁን። |
ከዚያም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የእስራኤልን ነገድ አለቆችና የእስራኤልን ጐሣዎች ሹማምት ሁሉ፣ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው።
ሙሴም ከእስራኤል መካከል ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠና፤ የሕዝብ መሪዎች፣ በሺሕዎች፣ በመቶዎች፣ በዐምሳዎች በዐሥሮች ላይም አለቆች አደረጋቸው።
እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አስፈሪው የእግዚአብሔር ቍጣ ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ ግደልና በጠራራ ፀሓይ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ስቀላቸው” አለው።
ስለዚህ እኔም የየነገዶቻችሁን አለቆች ጥበበኞችንና የተከበሩትን ሰዎች ተቀብዬ፣ ሻለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች እንዲሁም የየነገዱ ሹማምት በማድረግ በእናንተ ላይ ሥልጣን እንዲኖራቸው ሾምኋቸው።
ከርሱም ጋራ እያንዳንዱን የእስራኤልን ነገድ የሚወክሉ ዐሥር አለቆች ዐብረው ላኩ፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው ከእስራኤላውያን ጐሣዎች የተውጣጡ የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ።