ኢያሱ 8:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት፣ በከተማዪቱ ያገኙትን እንስሳትና ምርኮ ብቻ ለራሳቸው አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጌታ ኢያሱን ባዘዘው ቃል መሠረት የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ብቻ እስራኤል ለራሳቸው ዘረፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ለኢያሱ በነገረው መሠረት እስራኤላውያን በዚያች ያገኙትን የከብትና የሌላ ንብረት ምርኮ ሁሉ ለራሳቸው አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ሁሉ የእስራኤል ልጆች ለራሳቸው ዘረፉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው ቃል የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ እስራኤል ለራሳቸው ዘረፉ። |
በኢያሪኮና በንጉሧ ላይ ያደረግኸውንም ሁሉ፣ በጋይና በንጉሧ ላይ ትደግመዋለህ፤ በዚህ ጊዜ ግን ምርኮውንና ከብቱን ለራሳችሁ ታደርጉታላችሁ፤ ታዲያ ከከተማዪቱ በስተጀርባ የደፈጣ ጦር አዘጋጅ።”