በኬብሮናውያን በኩል በቤተ ሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ። በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜር በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል።
ኢያሱ 21:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሴቦንና ያዕዜር ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሴቦንንና መሰማርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ። |
በኬብሮናውያን በኩል በቤተ ሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ። በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜር በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል።
የሴባማ ወይን ሆይ፤ ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤ እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣ አጥፊው መጥቷል።
እጅግ ብዙ የሆነ የቀንድ ከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎች የነበሯቸው የሮቤልና የጋድ ነገዶች የኢያዜርና የገለዓድ ምድር ለከብት ምቹ ስፍራዎች መሆናቸውን አዩ።
ማለት በደጋው አገር የሚገኙት ከተሞች ሁሉና መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት በሙሉ ያካትታል። ሙሴ ሴዎንንና በዚያው ምድር ተቀማጭ የነበሩትን መሳፍንት፤ ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ የተባሉትን የምድያም አለቆች ድል አደረጋቸው።