ኢያሱ 21:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተራራማው በኤፍሬም አገርም ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም ከተሞች ሰጡአቸው፤ በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእነርሱም የተሰጡት አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ሴኬምና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚገኙት የግጦሽ መሬቶችዋ፥ ጌዜር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማርያዋን፥ ጌዜርንና መሰማርያዋን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰምርያዋን፥ ጌዝርንና መሰምርያዋን፥ |
ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋራ ዐብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።
ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ።