ኢያሱ 21:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ ሌሎቹ የእስራኤል ነገድ አባቶች ዘንድ ቀረቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዋውያን አባቶች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ነገዶች አለቆች ቀረቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሌዊ ነገድ ቤተሰቦች መሪዎች ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ የነገድ መሪዎች ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዊ ልጆች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ እስራኤልም ሕዝብ አባቶች ነገዶች አለቆች መጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዋውያን አባቶች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ነገዶች አለቆች ቀረቡ፥ |
የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው።
የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ።
እስራኤላውያን ከወረሷት ምድር ላይ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ከተሞች እያንዳንዱ ነገድ እንዳለው ድርሻ መጠን ይሆናል። ብዙ ካለው ነገድ ላይ ብዙ ከተሞች እንዲሁም ጥቂት ካለው ነገድ ላይ ጥቂት ከተሞችን ውሰዱ።”
ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል የየነገዱ ጐሣ አባቶች የደለደሉላቸው፣ እስራኤላውያንም በከነዓን ምድር የወረሱት ርስት ይህ ነው።
እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ መሪዎቹ ቀርበው፣ “ከወንድሞቻችን ጋራ ርስት እንድንካፈል እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞታል” አሏቸው። ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከአባታቸው ወንድሞች ጋራ ርስት ሰጣቸው።
እንግዲህ ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የየጐሣ መሪዎች ሴሎ ላይ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ ያደላደሉት ርስት ይህ ነው፤ የምድሪቱንም አከፋፈል በዚህ ሁኔታ ፈጸሙ።