ኢያሱ 17:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናሴ ነገድ ሴት ልጆች ከወንዶቹ ጋራ ርስት ተካፍለዋልና። የገለዓድ ምድር ግን ለቀሩት የምናሴ ዘሮች ተሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ስለወረሱ፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ስለሆነ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶች ዘሮቹ እንደ ወንዶች ዘሮቹ የርስት ድርሻ ስለ ተቀበሉ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ዘሮች ተሰጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ተቀብለዋልና፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ተቀብለዋልና፥ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና። |
ድንበራቸው ከመሃናይም አንሥቶ ባሳንን በሙሉ ይጨምርና፣ በባሳን ያሉትን ስድሳ የኢያዕር ከተሞች ሁሉ ይዞ የባሳን ንጉሥ የዐግን ግዛት ሁሉ የሚያካትት ሲሆን፣
የገለዓድን እኩሌታ፣ በባሳን የዐግ መንግሥት ዋና ከተማ የሆኑትን አስታሮትንና ኤድራይን ይጨምራል። እነዚህ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ዘሮች የተሰጡ ሲሆን፣ ይህም ለግማሾቹ የማኪር ልጆች በየጐሣቸው የተሰጡ ናቸው።
የምናሴ ርስት ከአሴር አንሥቶ ከሴኬም በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሚክምታት ይደርሳል፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በመዝለቅ በዓይንታጱዋ የሚኖረውን ሕዝብ ይጨምራል።
ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን ምድር ርስት ሰጥቷቸው ነበር፤ ለቀረው እኩሌታ ደግሞ ኢያሱ ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ከወንድሞቻቸው ጋራ ርስት ሰጣቸው። ኢያሱ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ባሰናበታቸው ጊዜ መረቃቸው፤