በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
ኢያሱ 15:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዓጽሞን በኩል አድርጎም ወደ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ይገባና መቆሚያው ባሕሩ ይሆናል። እንግዲህ በደቡብ በኩል ያለው ወሰናቸው ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዓጽሞንም አለፈ፥ በግብጽም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዓጽሞንም በመዝለቅ፥ በግብጽ ድንበር ላይ የሚገኘው ወንዝ፥ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይከተላል፤ ያም የድንበሩ መጨረሻ ይሆናል፤ እንግዲህ በደቡብ በኩል የይሁዳ ድንበር ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አጽሞንም ያልፋል፤ በግብፅም ሸለቆ በኩል ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቀርቃ ዞረ፥ ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፥ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። |
በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
በዚያ ጊዜም ሰሎሞን ዐብረውት ከነበሩት ከእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋራ፣ ማለትም ከሐማት መተላለፊያ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ካለው ምድር ከተሰበሰበው ታላቅ ጉባኤ ጋራ በዓሉን አከበረ። እነርሱም ሰባት ቀን፣ በተጨማሪም ሌላ ሰባት ቀን በድምሩ ዐሥራ አራት ቀን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በዓሉን አከበሩ።
“ድንበርህን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድረ በዳው እስከ ወንዙ ድረስ አደርገዋለሁ፤ በምድሪቱም ላይ የሚኖሩትን ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም አሳድደህ ከፊትህ ታስወጣቸዋለህ።
በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ፣ እግዚአብሔር እህሉን ይወቃል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
ከግብጽ በስተምሥራቅ ከሚገኘው ከሺሖር ወንዝ አንሥቶ፣ በሰሜን እስከ አቃሮን ወሰን ያለው አገር፣ ሁሉም እንደ ከነዓናውያን ምድር ይቈጠራል። ይኸውም በጋዛ፣ በአሽዶድ፣ በአስቀሎና፣ በጋትና በአቃሮን የሚኖሩትን የዐምስቱን የፍልስጥኤማውያን ገዦች ምድር የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም የኤዋውያን ምድር ነበር።
ከዚያም የአቅረቢምን መተላለፊያ በማቋረጥ በጺን በኩል እስከ ቃዴስ በርኔ ደቡባዊ ክፍል ይደርሳል፤ ደግሞም ሐጽሮንን ዐልፎ ወደ አዳር ይወጣና ወደ ቀርቃ ይታጠፋል፤
አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋራ፣ ጋዛ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋራ።