ኢያሱ 15:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ በአጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዐይን፥ ሪሞን፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልባዎት፥ ሺልሒም፥ ዓይንና፥ ሪሞን ተብለው የሚጠሩት በድምሩ ኻያ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙት ታናናሽ ከተሞችንም ሁሉ ያጠቃልላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላቦስ ሳሌ፥ ኤርሞትም ሃያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞን፥ ሀያዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ምድር ሁሉ ከጌባዕ አንሥቶ በኢየሩሳሌም ደቡብ እስካለችው ሪሞን ድረስ ተለውጣ ደልዳላ ሜዳ ትሆናለች፤ ኢየሩሳሌም ግን ከብንያም በር እስከ መጀመሪያው በር፣ ከማእዘን በርና ከሐናንኤል ግንብ እስከ ንጉሡ የወይን ጠጅ መጥመቂያ ድረስ በዚያው በቦታዋ ላይ ከፍ እንዳለች ትኖራለች።
ወሰኑም ከሴፋማ አንሥቶ ከዓይን በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ሪብላ ቍልቍል ይወርድና ከኪኔሬት ባሕር በስተምሥራቅ እስካሉት ሸንተረሮች ድረስ ይዘልቃል።